አርቲስት ዳዊት ፍሬው ኃይሉ “የኢትዮጵያዊነት አሻራ” የተሰኘ በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ የሲዲ አልበም ባለፍነው ሰኞ ምሽት በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት አስመርቋል።
አርቲስቱ በሙዚቃ መሳርያ ብቻ የተቀነባበረ አልበም አድማጮች ዘንድ ሲያደርስ ይህ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን፤ የሙዚቃ ስራዎቹ ያልተለመደና የሰውን ልብ መግዛት የሚችል መሆኑን የሙዚቃ ባለሙያዎች ይመሰክራሉ።
መሰል የሙዚቃ ስራዎች በአየር መንገድ እና ትላልቅ ሆቴሎች ብቻ መስማት የተለመደ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ አርቲስት ዳዊት ፍሬው ይዞት የመጣው የሲዲ አልበም ስራ የሙዚቃ አፍቃርያን በቦታዎች ሳይገደቡ እንዳሻቸው ማዳመጥ የሚያስችል እንደሆነም ተግሮለታል።
አርቲስት ዳዊት ፍሬው በአልበሙ ምርቃት ላይ ከአል ዐይን ኒውስ ጋር በነበረው ቆይታ፤ አዲሱ የሙዚቃ አልበም “መታሰብያነቱ ለ125ኛ የዓድዋ በዓል እና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደሆነ ተናግሯል።
ዳዊት ፍሬው አክሎ “የህዳሴ ግድብ ጉዳይ የሚታወቅ ነው ፤ያንን ወደ ህዝብ ማሻገር ደግሞ የኪነ ጥበብ ሚና ነው” ሲልም ነግሮናል። ሙዚቃው ከታሪክ ጋር የተያያዙ ትላለቅ ኃሳቦች እንዳምትም ነው ዳዊት የሚናገረው። ዳዊት ፍሬው የጥንታዊ ዜማ ስራዎችን በሉዩ ሁኔታ በዘመናዊ መልኩ በማቀናር እና በመስራት ለትውሊድ እንዲተላፍ የበኩሉን እተወጣ የሚገኝ አርቲስት ነው።
የዳዊት ፍሬው ከአባቱ አንጋፋው እርቲስት ፍሬው ኃይሉ የወረሰውን የሙዚቃ ልምድ የሙዚቃ ልምድ በአዲስ አበባ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ሙዚቃ በማጥናት አዳብሯል። “በልጅነቴ አባቴ ይዞኝ ወደ መድረክ ይሄድ ነበር ይህም ገና በልጅነቴ ወደ መድረክ እንድወጣ አስችሎኛል” ሲልም ነው ዳዊት የሚናገረው።